ልኡካኑ በሲቲ ዞን ላስደሬ የክፍያ መንገድ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የሶማሌ ክልል የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚንስትሯ ድሬዳዋ የገቡት ሔር ኢሴ በዮኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ ከ16-እስከ 17 በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረውን በአል ለመታደም ነው።
በአሉ በፓናል ውይይትና በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስቴድየም በድምቀት ይከበራል ሲሉ የበአሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ኢንጅነር ኡመር ዱዋሌ ገልፀዋል።
ይህን በአል ለመታደም ከጎረቤት ሀገራት ጅቡቲና ሱማሊያ በርካታ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል ብለዋል ።
ሔር ኢሴ ህዳር 26/2017 በፖራጓይ በተደረገው 19ኛው የዮኔስኮ ጉባኤ የማይዳስ የሰው ልጆች ወካይ የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።


