ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን የተለያዩ ሹመቶች እና ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቋል
ምክር ቤቱ አንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብትም አንስቷል።
በጉባኤውም ኢንጂነር ዑመር ደዋሌ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ተስፉ ፀጋ መራ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ ኮማንደር መሐመድ ኢብራሂም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ አቶ አህመድ አብደላ የአስተዳደሩ ምክር ቤት የህግ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ጣሂር ሮብሌን የድሬዳዋ አስተዳደር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ በማድረግ ሹመታቸውን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ለኮሪደር ልማቱ ማስፈፀሚያ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀትና ሁለት ረቂቅ ደንቦችን ተወያይቶ አጽድቋል።
በሌላ በኩል ባልተፈለገ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል በሚል የተጠረጠሩ አቶ አብደላ ሐሰን የተባሉት የምክር ቤት አባልን ያለመከሰሰ መብት በሙሉ ድምፅ አንስቷል።
በትዕግስት ቶሎሳ
ፎቶ፦ አገኘሁ ሸዋረጋ


