ዲያስፖራው በአገሩ ሁለንተናዊ እድገት ተሳትፎ እንዲያሳድግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የዲያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቶች የ2017 መጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማውን በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የዲያስፖራ አካላቶችን በማስተማር በድሬዳዋ አስተዳደር በኢኮኖሚው በማህበራዊ ጉዳዮች ተሳትፎ እንዲያደርጉ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አንባሳደር ፍፁም አረጋ ከለውጡ ማግስት በተለያዩ አለም ሀገራት የሚገኙ ዲያስፖራዎችን በማስተባበር በሀገራቸው ልማት እና በሀገራቸው የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መደረጉን ተናግረዋል።

የሁለተኛ ትውልድ ዲያስፖራ ንቅናቄ መርሃግብር በርካታ የዲያስፖራ እና ኢትዮጵያን ወዳጆች ያሰባሰበ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ማነቃቃት እንዲፈጠር ማስቻሉን ተናግረዋል።

የድረደዋ አስተዳደር ዲያስፖራ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ግርማ በበኩላቸው በባህር ማዶ የሚገኙ የድሬደዋ ወዳጆችና ተወላጆች ልየታ መደረጉን ገልፀው ስለ አስተዳደሩ በቀላሉ መረጃ ማግኝት የሚችሉበትን ዌብ ሳይት ተገንብቶ ስራ ላይ መዋሉ የዲየስፖራውን ተሳትፎ አንዲጠናከር እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

እንደሀገር ለዲያስፖራው የሚደረጉ ጥሪዎች የተጀመሩትን የልማትና የኢኮኖሚ መነቃቃት አንዲሁም የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ላይ ዲያስፖራዎች በአገሪቱ እየተመዘገቡ ለሚገኙ ለውጦች አካል እንዲሆኑ እያስቻለ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የ6 ወር እቅድ አፈፃፀማቸውን በገመገሙበት መድረክ የክልል ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የከተማ አስተዳደር ማስተባበሪያ ፅህጸት ቤት ኃላፊዎች ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በሚቀርቡት የ6ወር ሪፖርት ላይ በመመስረት ጠንካራ እና ደካማ ጎን በመለየት በቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ምስል፦ከንቲባ ጽ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *