“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ በአስተዳደሩ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኛ የብልፅግና ፓርቲ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በ01 ፣ 02 ፣ 03 እና 04 ወረዳዎች ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኛ የብልፅግና ፓርቲ አባላት የተዘጋጀው መድረክ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበት በተዋረድ ያሉት አባላቶች የተሻለ ግንዛቤ በመያዝ እና ህዝብን ለማገልገል ጠንካራ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተገልፃል።
በአስር ይዘቶች ተከፍለው የተዘጋጁት የመወያያ ሰነዶች ከቃል እሰከ ባህል ፣ ብሄራዊ ትርክት ማፅናት ፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ ስራ መስራት ሰላምን በሁሉም ክልሎች እና ከተሞች ውስጥ ማፅናት ፣ የፍትህ ዘርፉን ውጤታማነት ማጠናከር ፣ የሀገር ግንባታ ሂደት (Nation Building) ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም ኢኮኖሚያዊ ፍጥነትን ማረጋገጥ ፣ ማህበራዊ የብልፅግና ስራዎችን ማስጠበቅ ፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ማጠናከር ፣ በሲቪል ሰርቪስ ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ማረጋገጥ እና የሚዲያ ግንኙነት ማጠናከር በሚሉ አንኳር ነጥቦች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ዳዊት አያሌው
ምስል:- ዳዊት መስፍን


