“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገናሉ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር መድረኩ በዋነኝነት አመራሩ የፓርቲው አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን በተሟላ መልኩ ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንዲሁም ጥልቅ ግንዛቤ እና የጋራ አረዳድ እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከንቲባ ከድር አያይዘውም በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ አበረታች ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁ ሲሆን፤ መንግስት ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር በመፈጸም ቃልን ባህል ማድረግ መቻሉንም አመላክተዋል።
ለድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተዘጋጀው ስልጠና እየሰጡ የሚገኙት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ ናቸው።
ስልጠናው 10 በሚሆኑ የተለያዩ ይዘት ባላቸው ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ እየተሰጠ ይገኛል። ከቃል እሰከ ባህል፣ ብሄራዊ ትርክት ማፅናት፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ ስራ መስራት ሰላምን በሁሉም ክልሎች እና ከተሞች የውስጥ ሰላምን ማፅናት፣ የፍትህ ውጤታማነት፣ ሀገር ግንባታ ሂደት ዙሪያ፣ ኢኮኖሚያዊ ፍጥነት ማረጋገጥ ዙሪያ፣ ማህበራዊ ብልፅግና ስራዎችን ማረጋገጥ ይገባል የሚሉ ናቸው።
ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ማጠናከር፣ በሲቪል ሰርቪስ ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ማረጋገጥ፣ የሚዲያ ግንኙነት ማጠናከር ይገባል። በማለት የተዘጋጁት ሰነዶች ዙሪያ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ መካከለኛ አመራሮች በቀጣይ ጠንክሮ መስራት የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎችን ፍላጎት በማሟላት የሀገርን ብልፅግና እንዲያሳኩ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


