“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና በፓርቲ 2ኛው መደበኛ ጉባኤ ያሳለፉቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዋች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በድሬዳዋ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ሴክተር ተቋማት ለብልፅግና ህብረት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ መካሄድ ተካሄዶል።

በዚህም በአስተዳደሩ የሚገኙ ሴክተር ተቋማት፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤትና ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ጤና ቢሮ፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ለብልፅግና ህብረት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

በመድረኩም ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ ጉባኤው በርካታ ሀሳቦች የተነሱበት፣ ፓርቲውን ወደ ፊት ሊያሻግሩ የሚችሉ ውሳኔዎች የተላለፉበት አንደሆነ በውይይት መድረኮቹ ተነስቷል፡፡

በቀጣይም አቅጣጫዎችን ተረድቶ በመስራት በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲሰርፅ ማድረግ እና ለተፈፃሚነታቸዉ በትጋት መስራት አንደሚገባ ከሁሉም አባላት አንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ፡-አገኘሁ ሸዋረጋ

-ሙላለም ደሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *