ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዋች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በድሬዳዋ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ሴክተር ተቋማት ለብልፅግና ህብረት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።

በመድረኩም የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን፣ ማህበራዊ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በውጤታማነት ማስቀጠል፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን ማረጋገጥ፣ ጠንካራ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራ መስራት፣ የጠንካራ ፓርቲ ግንባታን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የብሔራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታን ማጠናከር፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ መስራት፣ የፍትህ ዘርፍ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የሀገር ግንባታን ማጠናከር የሚሉ ነጥቦችን የያዘ ሰነድ በመወያያነት ቀርቧል።

በቀጣይም አቅጣጫዎችን ተረድቶ በመስራት በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲሰርፅ ማድረግ እና ለተፈፃሚነታቸዉ መትጋት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *