እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ሮዛ ፓርክ እና ማልኮም ኤክስ ያሉ የሰብአዊ መብት መሪዎች ይታወሱበታል።
እንደ ጆርጅ ዋሽንግተን ካርቨር፣ ማዳም ሲ ጄ ዎከር እና ጋሬት ሞርጋን ያሉ ጥቁር የፈጠራ ሰዎች ዛሬም ታሪካቸው ይነገርበታል።
እንደ ማያ አንጄሉ፣ ጀምስ ባልድዊን፣ ቶኒ ማሪሰን ያሉ የጥቁር ባህል አቀንቃኝ ጥበበኞች ደግሞ ይወደሱበታል።
እንዲሁም እንደነ ባራክ ኦባማ፣ ካማላ ሃሪስ እና ኔልሰን ማንዴላ ያሉ ጥቁር የፖለቲካ መሪዎች በዚህ ወር ይታሰባሉ።
ወሩ የጥቁሮችን ፍትሕ፣ የጥቁሮችን ጤና እና ደኅንነት፣ የጥቁሮችን ሰብዓዊ መብት እና የጥቁሮችን የእኩልነት ጥያቄ የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ ይከበራል።


