“በመጪው የረመዳን ወር ጾም ህዝበ ሙስሊሙ አቅመ ደካሞችን በመርዳት በጎ ተግባራትን በማከናወን ሊያከበር ይገባል” የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

የ1446ኛው የረመዳን ወር ፆም ከ6ቀናቶች በኃላ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

30ኛው የምርኩዝ መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ መሻኢኾች ፣ኢማሞች፣ኡስታዞች በተገኙበት በተለያዩ የእስልምና ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

በመርሀ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካይ ኡስታዝ አብደላ በንግግራቸው የምርኩዝ መድረክ ወደ ድሬዳዋ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ ለ1446 ዓ.ሂ የረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በፆምና ጸሎት የሚያሳልፈው የረመዳን ወር በረከት የሚያስገኙ መልካም ነገሮችን በመስራት ሊያሳልፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት “በጎ ተግባራትን በማከናወን ከፈጣሪ ረሀመት ሊያገኝ ይገባል ብለዋል ።

የጾሙን ወቅት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመንከባከብ ሊያሳልፈው ይገባል ሲሉም ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጥሪ አቅርበዋል።

ያነጋገርናቸው የመድረኩ ተሳታፊዎችም ሲገልጹ 30ኛው የምርኩዝ መድረክ የረመዳን ወር ጾም ለመቀበል በዝግጅት ላይ ሆነን መካሄዱ ይበልጥ እንዳስደሰታቸው እና ጾሙን በንጹህ ልቦና በይቅርታ ለመጀመር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በመርሀግ ብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣የሀገር ሽማግለዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

ሰላም ለማ

ምስል፦ አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *