#DGC የካቲት 17/2017
ጉብኝቱም በዋናነት በአስተዳደሩ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልክቶ ድጋፍ ና ክትትል ለማድረግ ታስሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል ።
በድጋፋዊ ጉብኝቱም ከተረጂነት ለመውጣት በሚደረጉት ጥረት ውስጥ በ5 ጉዳዮችበመግባባት፣በማዘጋጀት፣በማጥራት፣በማቀናጃት እና በማሻገር ላይ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ተደርጎ ምልከታው እንደሚካሄድ
፧የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ አስረድተዋል።
በዚህም በዋሂል ወረዳ አስተዳደር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአትክልት ና ፍራፍሬ፣በሰብል ምርት በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርተው በተጨባጭ ህይወታቸውን መቀየር የቻሉ አርሶ አደሮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በወረዳውም በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጭ መሆናቸውን ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።
በቀጣይም የአሰራር ስልቶች በመጠቀም ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት በዘላቂነት በመላቀቅ ከተረጂነት ነጻ ሞዴል ቀበሌዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት ተደርጎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በጉብኝቱም የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ የዘርፉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ሰላም ለማ
ምስል፦ ሰላም አበበ ና ሙሉዓለም ደሴ


