ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመልክዓ ምድራችን የተስማሙ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ ድሮኖችን በራስ አቅም ማምረት መቻሉን አስታወቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለመልክዓ ምድራችን የተስማሙ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙድሮኖችን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ማምረት መቻሏን ገለጹ።

አሁን ላይ የጦር ቴክኖሎጂ 4ኛ ትውልድ ላይ ደርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን የሚመጥኑ የጦር ቴክኖሎጂ ውጤቶች በሀገር ልጆች ማምረት ተችሏል፤ ይህም ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአፍሪካውያን ጭምር የሚያኮራ ነው ብለዋል።

ጦርነት ለማስቀረትም ሆነ በአጭር ጊዜ ለመጨረስ ዝግጁነት ትልቅ ሚና አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን መሰል ስራዎች ለዚህ ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ምርምር እና ፈጠራን በማጠናከር ለሀገር ውስጥም ሆነ ለሽያጭ የሚመረቱ ድሮኖችን ይበልጥ ማዘመን እና ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከሰሞኑ በመከላከያው ዘርፍ ያየናቸው ለውጦች ኢትዮጵያ እያንሰራራች መሆኗ ማሳያ ናቸውም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

ይህን እድገት ለማዝለቅ ቀጣይነት ባለው የምርምር ሥራ ላይ፣ ገበያ በማስፋት ተግባር ላይ እና በሀገር ውስጥ የስማርት ሴንሰር ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)።

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *