የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የትንሳዔ በዓልን በድሬ ዳዋ አለም አቀፍ ስተታዲየም አከበሩ።
በስነ-ስርዓቱ የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ሰብሳቢ ፓስተር ሚኪያስ ታየ ይህ በዓል በወንጌላውያን በአመት ከሚከበሩት በዓላት መካከል ትልቁና ዋነኛው መሆኑን ጠቅሰው የሰው ልጅ በሃጢዓተኛነቱ የተወሰነበትን ሞት እየሱስ ጌታ መስዋዕት ሆነው ዳግም ከሞት የተነሳበትን ቀን የምናስታውስበት ነው ብሏል።
በባዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በእምነት ብንለያይም ያለንን ወንድማማችነታችንና አብሮነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር በየእምነታችን ብጋራ በመሆን በምናከብራቸው በዓላት አንድነታችንን ይበልጥ እናጠናክራለን ሲሉ ተናግረዋል።
በጎም ሆነ ክፋት ትርፉ ለራስ ነው ያሉት ክቡር ከንቲባው ሁላችንም በየእምነታችን የታዘዝነውን በጎ ስራ ውስጥ ያለው ለሌለው በማካፈል ድሃውን በማብላትና በማልበስ ባዓሉን በጋራ በማክበር ሁሉም ደስታውን እንዲካፈል መልዕክቱን እስተላልፏል።
በበዓሉ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ ፣ ከድሬ ዳዋ የውንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ የእምነት አባቶች ፣ ፓስተሮች ፣ የምነቱ ተከታዮችና እንግዶች ተገኝተዋል
በኤልያስ አሜ


