በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የስልጠና መድረኩ ዋነኛ ዓላማ የአመራሩን አቅም ለመገንባት መሆኑን በመግለፅ፤የማህበረሰቡን ጥያቄ በተገቢው መንገድ የሚመልስ እንዲሁም በእውቀት የሚመራ አመራር ለመፍጠር ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ክቡር ከንቲባ ከድር መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ለስልጠናው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በበኩላቸው አመራሩ ሀገራዊ እንዲሁም ደግሞ አህጉራዊና ተለዋዋጭ የሆነውን አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ እንዲገነዘብና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ችግሮችን ተረድቶ ለመፍታት የስልጠና መድረኩ ጉልህ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።
አቶ ኢብራሂም አያይዘውም ከዚህ ቀደም የአመራሩን የአቅምና የክህሎት ክፍተት የሚሞሉ ስልጠናዎች በተለያየ ጊዜ መሰጠቱን ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለት የተጀመረው የስልጠና መድረክም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በጠዋቱ የስልጠና መርሀ-ግብር የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት በሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ አመራሩን የሚያነቃቁና ለውጡን እንዲያቅ የሚያስችሉ inspire, engage, achieve: motivational training for team success በሚል ሰነድ የቀረቀ ሲሆን በከሰዓቱ መርሀ ግብርም በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


