የድሬደዋ ወጣቶች ምክር ቤት ከብክለት ወደ ኃብትነት የአሸዋ ዳርቻ የወጣቶች ልማት ፕሮጀክት እየተገበረበት በሚገኝው ስፍራ በዛሬው እለት ከወረዳ ወጣት ምክር ቤት እና ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን የፅዳት ዘመቻ አካሔዷል ።
በእለቱም ከጽዳት ዘመቻው በተጨማሪ ወጣት ምክር ቤቱ እየተገበረው ባለው ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለሆኑ ወጣቶች በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጀዋር የፅዳት መርጃ ግብአት ድጋፍ ተደርጓል ።
ክቡር ከንቲባውም ባስተላለፉት መልክት ወጣት ምክር ቤቱ የወጣቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎን ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በአሁን ሰዓትም አሸዋን ፅዱና ውብ ለማድረግ ወጣቶችን በማደራጀት የአከባቢውን ፅዳት እየጠበቁ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ በመመቻቸቱ ድሬዳዋን ፅዱና ውብ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚደግፍ በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያድርጉ ገልፀዋል ።
በተጨማሪም በአከባቢው የተሰማራው የንግድ ማሕበረሰብ የተደራጁትን ወጣቶች ከመደገፍ ባለፈ አከባቢውን ፅዱና ውብ ለማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ የስራው አንድ አካልና ባለቤት በመሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አሳስበዋል ።
በእለቱም በተካሔደው የፅዳት ዘመቻ ላይ ክቡር ከንቲባ፣ የአስተዳደሩ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ፣ የወጣት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፣ የወረዳ አመራሮች ፣ የፖሊስ አባላት ፣ የወጣት ምክር ቤት አባላት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች ፣ የንግዱ ማሕበረሰብ እና የአከባቢው ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ክብሩ ከንቲባው የተሰሩ ስራዎች እና በአከባቢው ወጣቶች የተጀመሩ የስፖርት ማዞተሪያ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል ።
ድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት


