ተቋማት ሰው ተኮር የሆነ አግልግሎት በመስጠት ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ተጠቆመ

በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት አንፃር ከተገልጋዮቻቸው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችላቸው መሰው ተኮር አገልግሎት እቅድ በማዘጋጀት እንዲተገብሩ በመደረግ ላይ ሲሆን ከብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተውጣጡ የሱፐርቪዥን ቡድኖች የተቋማትን የ2017 በጀት አመት የ3ኛው ሩብ አመት የሰው ተኮር አገልግሎት እቅድ አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ ሱፐርቪዥን ማካሄድ ጀምረዋል።

የሱፐርቪዝኑ ዋንኛ አላማም ተቋማቱ ከእቅድ አንፃር ያስመዘገቡትን አፈፃፀም በመፈተሽ የታዩ መልካም ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና የሚታዩ ውስንነቶችን ለይቶ በማሳየት በቀጣይ እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ሲሆን በዋናነትም ተቋማት ሰው ተኮር የሆነ አግልግሎት በመስጠት ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ነው የተገለፀው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ ወረዳ 02፣ ወረዳ 04 እና ወረዳ 09 እስካሁን ሱፐርቪዥኑ የተደረገባቸው ተቋማት ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ተቋማት ሱፐርቪዥኑ ተጠናክሮ የማቀጥል ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *