የካብኔ ውሳኔዋች

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዋች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

1ኛ፦ካብኔው በመጀመሪያ አጀንዳው የ10 አመት(2025-2035 እ.እ.አ) ኢንዱስትሪ ሮድ ማኘ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል ።

በውይይቱም ነባር ኢንዱስትሪዋች ከፍ ማድረግና በቁጥርም እንዲጨምሩ የማድረግ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዋች እንዲገቡ ማድረግ። ከውጭ የሚገቡ ጥሬ ምርቶችን ምንዛሬ በመቀነስ ጥራት ያለው ምርት በማምረት ወደ ውጭ በመላክ ምንዛሬ እንዲያመጡ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን መጠቀም እና በኢንድስትሪዎች የስራ እድል መፍጠር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ካቢኔው ትኩረት ሰጥቶ በመወያየት የኢንዱስትሪ ሮድ ማኘ አፅድቋል።

2,ካብኔው በነበረው መደበኛ ስብሰባው የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት እና የግል አጋርነት ለማጠናከር በወጣው ደንብ ላይ ተወያይቶ ደንቡን አፅድቋል።በቀጣይ ደንቡ ተፈፃሚ እንዲሆን በአስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ የሚፀድቅ ይሆናል ።

3,የቦረን እና የገንደ ሪጌ ኤል .ዲ.ፒ (LDP)ጥናት በኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ አማካኝነት ተጠንቶ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ረቂቅ ጥናት ላይ ከገንደ ሪጌ ጋራ ላይ የሚወርደው የጉርፍ ውሀ በአካባቢው እያደረሰ ያለውን ችግር ለመከላከል የጎርፍ መከላከያ ለመስራት ሀሳብ የያዘ ሲሆን ካብኔው በጥናቱ ላይ ተወያይቶ ልማቱ ተፈፃሚ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ስለሚነኩ መኖሪያ ቤቶች፣በከፊል የሚነኩ እንዲሁም ተለዋጭ ቦታዋች እነዚህን መሰል ችግሮችን በመሬት ልማትና ማነጅመንት ቢሮ እና የኮንስትራክሽን ልማት ቢሮ በጋራ አጥንተው እንዲያቀርቡ ወስኗል።

4,ካብኔው በመሬት ልማት ማነጅመንት ቢሮ የነበረውን የባለጉዳይ እንግልት ለመቀነስ እና የነበረውን መረጃ አያያዝ ለማዘመን የመሬት ዲጂታላይዜሽን ሶፍትዌር ተግባራዊ ለማድረግ ተቋሙ የስምምነት ፊርማ ተፈራርሞ ወደ ተግባር እንዲገባ ውሳኔ አሳልፉል።

በመጨረሻ ካቢኒው በሌሎች አጀንዳዋች ላይ በመወያየት ውሳኔዋችን አሳልፉል

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *