የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የፋይናንስ ውስንነት የገጠማቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ከማድረግ አንስቶ በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማ ሆነ በገጠር እየሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪም በሀረር እና በጂጂጋ ቅርንጫፎቹን በመክፈት ዘመኑን የዋጀ ዲጂታል ፋይናንስን በመተግበር የፋይናንስ አገልግሎቱን ፈጣን ፣ ቀልጣፋ እንዲሁም ደንበኛ ተኮር በሆነ መልኩ እየሰጠም ይገኛል ።
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፎቹን በማስፋት በዛሬው እለትም የገንደገራዳ ቅርንጫፍን በይፋ አስመርቋል ። በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተሾመ አበበ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ገንደ ገራዳ ቅርንጫፍ ደንበኞቹን ለመድረስ ፣ የነዋሪውን ህብረተሰብ የፋይናንስ አገልግሎቱን በስፋት ተደራሽ የማድረግ የተቋሙ የፀና አቋም ሁሌም በትጋት የማገልገል እና በላቀ ቁርጠኝነት የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች የመንቀሳቀስ ብሎም የድሬዳዋ አስተዳደር የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የስራ አመራር ቦርድ የማይቋረጥ ድጋፍ እና ክትትል መሆኑንም ነው የተናገሩት ።
አቶ ተሾመ አክለውም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በቀጣይም ተደራሽነቱን በማስፋት የሚሰጠውን አገልግሎት እያሳደገና ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች ጋርም እራሱን እያወዳጀ በስፋት እንደሚሰራም ነው በእለቱ ያስታወቁት።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአገኘው ሸዋረጋ


