በዚህም በጠዋቱ መርሀ-ግብር በብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) በቀረበው የስልጠና ሰነድ ላይ ሰልጣኞች በቡድን በመከፋፈል ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያም በቀጣይ የሚዲያና የኮምኒኬሽን እንዲሁም የህዝብ ግንኙነት ስራዎች እንዴት ማከናወን ይገባል የሚለው ሀሳብ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ማብራሪያ ሰተው የዛሬው የስልጠና መርሀ ግብር ተጠናቋል።
ስልጠናው በነገው እለት በሌላ ርዕሰ ጉዳይ የሚቀጥል ይሆናል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሰላም አበበ


