ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን 7 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑንምና በቀጣይም በህገ-ወጥ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ንግድ ቤቶች ላይ የሚደረገዉ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል ።
በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሳቢያን ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ዋ/ኢ/ር አንበሉ አየለ ለድሬ ፖሊስ ሚዲያ እንደገለፁት አስቀድሞ በተከናወነ መረጃ ማሰባሰብን ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማዎች መሰረት በማድረግ ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በወረዳው ላይ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በተከናወነ የተቀናጀ ስኬታማ ኦፕሬሽን ስራ በማከናወን በተደረገ ብርበራ 32 የሺሻ ማጨሻ ጠርሙስ ፤ 49 ፍሬ ቡሪ፤ 50 ገመድ ፣115 ፒፖ ፣24 ቀስቲር እንዲሁም 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን ገልፀው ይህ የተቀናጀ ኦፕሬሽን በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
በተያያዘ ዜና ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድሬዳዋ ከተማ ወረዳው የተለያዪ አካባቢዎች በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ ለጥቁር ገበያ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለፁት ጣቢያው አዛዡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን 2 ግለሰቦችና ባለ2 ሌትር ሀይላን ኮዳ 25 ፍሬ ባለ 25 ጄሪካን 3 ፍሬ በጠቅላላው 109 ሌትር ቤንዚልና በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑና በቁጥጥር ስር የዋለውን ነዳጅና ለሚመለከተው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንደሚያስረክቡ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ተናግረው ።
ለዚህ ኦፕሬሸን ውጤታማነት ማህበረሰቡ ፣የወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት፣የመረጃና ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት የአድማና ልዩ ሁነት ዲቪዥን አመራርና አባላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዉ ህብረተሰቡ በመሰል ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን ለህግ በማቅረብና በህገ ወጥ ድርጊቶች ምክንያት በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የጤና ፣ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያና አካበቢያዊ ጉዳችን በመከላከል ረገድ ማህበረሰቡ ከፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር አጋርነቱ ማሳየት እንዳለበት መልዕክታቸውን ጨምረው አስተላልፈዋል ።
መረጃው የድሬ ፖሊስ ነው


