ውይይቱ በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ስር ካሉ ጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንዲሁም ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ጋር የተደረገ ሲሆን ይሄንኑ ውይይት በአራት የመወያያ ማዕከላት በቀረበው “የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት!” በሚል መሪ ቃል የቀረበውን ፅሁፍ መሰረት በማድረግ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ አመራሮች ተሳታፊዎችን በየመወያያ ማዕከላቱ አወያይተዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ የጤናው ሴክተር አርበኝነት ለሀገር ዕድገት ካለው አንፃር በደንብ መታየት ያለበት ነው ሲባል ይህ ከአባቶቻችን ካለፈው ታሪክ ተምረንና አባቶቻችን ያለ አንዳንች ዘመናዊ መሳርያ ጠላትን የህይወት መሰዋትነት ከፍለው ታርክ እንደሠሩ ሁሉ የጤና ባለሙያም ክቡር የሆነውን የሰውን ህይወት ለመታደግ ማንኛውንም መሰዋትነት በመክፈል አርበኝነቱን ማስቀጠል እንዳለበትና ባለሙያው አሁን ላለው የኑሮ ውድነት እና ውስብስብ ችግሮች ሳይንበረከክ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለው አገልግሎት እንደ አስተዳደሩ እውቅና የሚሰጠውና ችግሮች እንዳሉ የሚያውቅ ሲሆን ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ይሠራል ተብሏል።
በዚህ የውይይት መድረክ በአራቱም የመወያያ ማዕከላት ከ 1200 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
#ምንጭ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት


