የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና እና በእውነት “

በድሬዳዋ አስተዳደር “የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና እና በእውነት “በሚል መሪ ቃል ለአመራሮች፣ ለሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ ።

በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ብልፅግና ፓርቲ በለውጥ ስራዎች ያስመዘገባቸውን በርካታ ውጤቶች በማስተዋወቅ እንዲሁም በንቅናቄ በህዝብ ግኝኙነት ስራ በማጀብ ህብረተሰቡን ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለልማት በማነሳሳት ረገድ ወሳኝ የሆነ የህዝብ ግኝኙነት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡

ክቡር ከንቲባ ከድር አያይዘውም የዲጂታል ሚዲያውን በአግባቡ የተረዳ በቂ ክህሎትና ዕውቀትን የታጠቀ ጠንካራ ኮሚኒኬተር ለመፍጠር ይህ የስልጠና መድረክ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው በማመላከት አሁን ባለንበት ጊዜ አንዳድ የማህበረሰብ ክፍሎች አጀንዳ ተቀባይ ከመሆን ይልቅ አጀንዳ ፈጣሪ በመሆን ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም በተለይም በሶሻል ሚዲያው ላይ በርካታ የሀሰት መረጃዎች እንደሚያሰራጩ በመግለፅ፤ ይህንን ለመመከትና እውነታውን ለህዝብ ለማድረስ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

በመጨረሻም ከንቲባ ከድር በዘመናዊ ሚዲያ የትግል መስክ ላይ በንቃት በመሳተፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት ከስልጠናው የምታገኙትን እውቀት በመጠቀም በቀጣይ የፖለቲካ ኮሚኒኬሽን መልዕክት ቀረፃ ላይና አጀንዳ ተከላ ላይ በሚዲያ ላይ የበላይነት ከመውሰድ ባሻገር በጸረ ሰላም ሀይሎች ላይ ተፅኖ ፈተጣሪ ኮሚኒኬሽን መሆን ይገባል ሲሉ ለሰልጣኞች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ማግስት በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች ተጨባጭ እምርታን በማምጣት በህዝብ ዘንድ ተስፋ የተጣለበት የለውጥ ጉዞ ፍሬ ያፈራ ዘንድ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል ሲሉ የተናገሩት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው። አቶ ኢብራሂም አያይዘውም እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

ስልጠናውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) እየሰጡ ይገኛሉ።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *