የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) የተመራው ሉዑክ ቡድን በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል

ልዑካን ቡድኑ በአስተዳደሩ ወጪ የተገነባውን የሲቪክ ሴንተር ማዕከልን፣የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ከመደመር መጽሀፍት ሽያጭ በተገኝ ገቢ የሚገነባውን የእምርታ ቤተመጽሀፍትን ተመልክተዋል። አማ የምግብ ዘይት ፋብሪካ፣በማምረቻ ሼዶች የመማሪያ መጽሀፍት ህትመት እንዲሁም ለኮሪደር ልማት ግብዓት የሚውሉ ልዩ ልዩ የማምረቻ ሼዶች ጓብኝተዋል።

በአስተዳደሩ በባለፉት የለውጥ አመታት ፤በስራ እድል ፈጠራ በቴክኖሎጂ እየተከናወኑ የልማት ስራዎች የአስተዳዳደሩን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገልጸዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግም ባለሀብቱን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ በማሰማራት ከውጪ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ በመተካትና ገበያን በማረጋጋት በኢኮኖሚ ዘርፍ አንጸባራቂ ድል መመዝገባቸውን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ክቡር ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል።

በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

ሰላም ለማ

ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *