የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በ13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማ ገቡ

እንግዶቹ በድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዮናስ በትሩ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በተጨማሪም እንግዶቹ በከተማዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እንዲሁም ሻምፒዮናው የሚካሄድበት ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጎብኝተዋል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ

Read More

በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና እንደቀጠለ ነው::

በዶክተር ኢብሳ መሀመድ ወይም ደሚና አማካኝነት ትውልድ ላይ ከመስራት እና ከመገንባት አኳያ እንዲሁም አመራሮች በስራም ሆነ በተለያዩ አካባቢዎች ያላቸውን የኮሚዩኒኬሽን አግባባቸውን ማሳደግ በሚገባቸው ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመድረኩ ፅሁፍ አቅራቢው ነባራዊ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ምሳሌዎችን በማጣቀስ ስልጠናውን ሰጥተዋል። በአጠቃላይም በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። በአለማየሁ አበበ ፎቶ…

Read More