እንግዶቹ በድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዮናስ በትሩ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪም እንግዶቹ በከተማዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እንዲሁም ሻምፒዮናው የሚካሄድበት ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጎብኝተዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ቴድሮስ ልዑልሰገድ


