116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓል በአስተዳደሩ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መመሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መገራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመላው የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት አመራር እና አባላት ለ116ኛው የፖሊስ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓል በአስተዳደሩ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል።

“ለተለወጠ ሀገር ያደገ ፖሊስ!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ ቀን ሲከበርም በዋናነት ፖሊስ በባለፉት በርካታ አመታት ውስጥ ለሀገር፣ለህዝብ ሰላምናደህንነት እንዲሁም ፍትህን ለማረጋገጥ የከፈላቸውን መሰዋትነት በመዘከር መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉን በአስተዳደሩ በደማቅ መርሃ ግብር ለማክበርም በርካታ የፖሊስ ሰራዊት አባላት የሚሳተፉበት ስፖርታዊ ውድድሮች ከግንቦት 24 ቀን ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ግንቦት 30 በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስቴዲየም በደማቅ ወታደራዊ ትርኢቶች ይጠናቀቃል

ሌላው የፕሮግራሙ አካል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መመሪያ በባለፉት አመታት ያለፈበትንና ከለውጡ በኃላ ያስመዘገባቸውን ስኬት የሚዳስስ ጥናታዊ ጹሁፍ እንዲሁም የፎቶ አወደ ርዕይ የሚካሄድ መሆኑን ተገልጿል።

ስለዚህ መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ በፕሮግራሞቹ ላይ በመገኘት ለፖሊስ ያለውን ድጋፍ እንዲያሳይም ጥሪ ቀርቧል።

ሰላም ለማ

ምስል፦ አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *