የንግድ ማህበረሰብ ሚና ለሀገር እድገት ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የወረዳ 08 አስተዳደር ፅህፈት ቤት በገቢ ፣ በንግድ ፣ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር በዛሬው እለት ውይይት አካሂዷል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የልማት ስራዎች ከመሰራታቸውም በላይ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካው መስክ ውጤታ የሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ አጠቃላይ የልማት ስራዎች ከግብ እንዲደርሱም የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበትም ከመድረኩ ተገልፆል ።
ኮንትሮባንድን ጨምሮ ህገ-ወጥ ንግዶችን በጋራ በመሆን ከመከላከል በዘለለ ለአንድ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ ያለውን ግብር በወቅቱ በመክፈል ለሀገራችን ብሎም ለአስተዳደሩ እድገት እና ብልፅግና በጋራ በመሆን መስራት እንደሚገባም ነው በወረዳ 08 አስተዳደር በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የተገለፀው ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :-እዮኤል


