መርሀ ግብሩንም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተወካይና የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አሊይ ከጤና ባለሞያዎች ጋር በጋራ በመሆን ለገሀሬ በሚገኘው አልመርከዝ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አስጀምረውታል።
በዚህም ኢንጂነር ሳጅድ ብልፅግናን ከማረጋገጥ አንፃር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆንን ገልፀው በተለይም፤ በጤናው ዘርፍም ተደራሽነትን ብቻ ሳይሆን ቀድሞ መከላከልን መሰረት ያደረጉ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢንጂነር ሳጅድ አያይዘውም የፖሊዮ በሽታ ህፃናትን የሚጎዳ በመሆኑ ህፃናት ጤናቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ክትባቱን መከተብ እንደሚገባቸው አመላክተው፤ በአስተዳደሩም ከ83 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህፃናት ክትባቱ እንደሚሰጥ በመግለፅ ሁሉም ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ በድሬዳዋ አስተዳደር በገጠርም በከተማም የሚገኙ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን 100 ፐርሰንት ለመከተብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሰላም አበበ


