የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም ነው በውይይቱ የተገለጸው።
በዋናነት የንግዱ ማህበረሰብ በባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች የሚታዩበት፣ በአምራች ኢንዱስትሪው የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችንን ለመቅረፍ የሚሰራበት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መሆኑን ተመላክቷል።
የመድረኩ ተሳታፊ የንግዱ ማህበረሰብም በውይይቱ ወቅት አስተያየታቸውን እንደገለጹት በንግዱ ዘርፍ በምርት አቅርቦት መካከል ያለውን ችግር በመፍታት የህበረተሰብ እርካታን ና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ አስተዋዕኦ እንደሚያበረክቱ ጠቁመዋል።
ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የተካሄደው የውይይት
መድረክ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮችም ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰዋል።
ሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


