የካቢኔ ውሳኔ

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዋች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

1ኛ:- ካቢኔው የድሬዳዋ አስተዳደር የባህል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋምና እዉቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል

በወጣዉ እረቂቅ አዋጅም ማህበረሰቡ በአካባቢው በሚቋቋመው የባህል ፍርድ ቤት በቋንቋቸው፣በባህላቸው እንዲሁም በሀይማኖታቸው እንዲዳኙ ከማድረግ ባሻገር ቂም ከመያያዝ ወደ ቀድሞ ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ለማስቻል እንደሚያግዝ በቀረበው እረቂቅ አዋጅ የቀረበ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል ።ሰነዱ ለአስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀቅ ካብኔው ውሳኔ አሳልፋል።

2ኛ:- የአስተዳደሩ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያቀረበዉን የከተማ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ታረፍና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፉል

ካብኔው በውይይቱ አሁን ያለውን የዶላር እና የኤሌክትሪክ እንዲሁም ሌሎች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በተቋሙ ላይ የሚፈጥሩትን ጫና ተወያይቶ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ነገር ግን ማሻሻያው የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ አንዲሆንና አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ተቋሙን መደጎም እንዳለበት እና በወር እስከ 250 ጄሪካን የሚጠቀሙ የማህበረሰብ ክፍሎች ቀድሞ ከነበረው 38 ሳንቲም ወደ 49 ሳንቲም፣በወር 500 ጄሪካን የሚጠቀሙ የማህበረሰብ ክፍሎች 44 ሳንቲም ወደ 56 ሳንቲም ፣በወር 750 ጄሪካን የሚጠቀሙ ከ62 ሳንቲም ወደ 80 ሳንቲም ከፍ እንዲል ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፋል

3ኛ:- በአስተዳደሩ የአንድ ማዕከል አገልግሎት (MESOB) ተግባራዊ ለማድረግ ቀደም ሲል በግለሰብ ህንፃ ተከራይተው በተበታተነ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ሲቨል ሰርቨሱ ለተቋማት በሰጣቸው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት የማህበረሰቡን እንግልት ለመቀነስ ዓብይ ኮሚቴና ቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም ለሥራዉ አስፈላጊ የሚሆን ህንፃናዎች እና አስተዳደሩ ያስገነባው ባለ አምስት( 5 )ወለል ህንፃ ጨምሮ ግብዓት እንዲሟላላቸው እንዲሁም በ2018 በጀት አመት አዲስ ለመንግስታዊ አገልግሎት የሚሰጥ ህንፃ እንዲገነባ ዉሳኔ አሳልፋል።

በመጨረሻ ካቢኒው በሌሎች አጀንዳዋች ላይ በመወያየት ውሳኔዋችን አሳልፉል

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *