#የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ሃምሌ 21 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፦
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ሃምሌ 21 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ፣ በምርት አቅርቦትና የገበያ መረጋጋት ስራዎች እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል።
1ኛ :-የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ጋር በተያያዘ እንደ አስተዳደር 1.5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በእቅድ የተያዘ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ውሃ ገብ በሆኑ ስፍራዎች እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎች በሚኖርባቸው እንደ ትምህርት ቤቶች ፣ ጤና ጣቢያ እና የወጣቶች አካዳሚ ላይ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ከሃገር አቀፉ መርሃግብር ጋር በተቆራኘ መንገድ ሊሰራ እንደሚገባ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
2ኛ፡- የምርት አቅርቦትና የገበያ መረጋጋት ስራዎች ዙሪያ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በተሻለ ቁጥጥር ማጠናከር ፣ የሸማች ማህበራቶችን ከሌሎች ክልሎች ተሞክሮዎችን በመውሰድ መደጎምን ጨምሮ ከመሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የአስተዳደሩ የንግድ ጽህፈት ቤት ሼዶችን በማዘጋጀት ምርትን በፋብሪካ ዋጋ አቅርቦት እንዲፈፀም በሚሉ ሃሳቦች ዙሪያ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ካቢኔው ከዚህም በተጨማሪ በስራ እድል ፈጠራ እና በተለያዩ አጀንዳዋች ላይም በመወያየት ወሳኔዋችን አሳልፏል።


