ኢፊድሪ ፌድሬሸን ምክር ቤት ከUNDPጋር በመተባበር የተዘጋጀ የምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የመንግስታት ግኑኝነት እና የሰላም ግንባታ የመክክር መድረክ ተኳሂዷል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ምክክሩ አጎራባች ክልሎች እና አስተዳደሮችን በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር፣ በአሠራር ሥርዓትና አደረጃጀት በማዋቀር ግጭቶችን በሰላማዊ እና በዘላቂነት ለመፍታትና በአጠቃላይ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል በመስረኩ ላይ ገልጸዋል።
የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን በተለይ ከአዲስ አበባ – አዳማ – ሚኤሶ – ድሬዳዋ ተጎራባች ክልሎችን ከሚያስተሳስረው መንገድ በተጨማሪ ከአዲስ አበባ – ጅቡቲ የሚዘልቀው የባቡር ትራንስፖርት የእርስ በእርስ ትስስርን ፣ የንግድ ትስስርን ፣ የባህል ልውውጥና መስተጋብርን የፈጠረ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ዛህራ ኡመድ እንደተናገሩት ፌዴራላዊ ስርዓተ መንግሥት አንዴ ተሠርቶ የሚጠናቀቅ ሳይሆን፣ በረጅም የግንባታ ሂደትና በትውልድ ቅብብሎሽ የሕገ መንግሥታዊነት መሠረቱን እያሰፋና እያጠነከረ የሚሄድ መሆኑን አመላክተዋል።
ወ/ሮ ዛህራ አያይዘውም የተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር እና የትብብር ፎረም ተቋማዊ ማድረግ በቀጠናው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለመገንባት ፣ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ፣ በአሠራር ሥርዓትና አደረጃጀት በማዋቀር ግጭቶችን በሰላማዊ እና በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የአምስቱ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊዎች ፣ የክልል ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ሃላፊዎችን ጨምሮ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰላም ሚንስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።


