በአስተደደሩ የሚገኙ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ተገለፀ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ እና በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጂኑር የተመራ ቡድን በአስተዳደሩ የከተማ ወረዳዎች ድንገተኛ ምልከታ አደረገ። የምልከታው ዋንኛ አላማ በወረዳዎቹ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ነባራዊ ሁኔታ በአካል ተገኝቶ ለመመልከት እና በተለይም የተገልጋይ ቀን ተብለው በሚታወቁት እለተ ሰኞ…


