በጉብኝታችን የክልሉ መንግስት ሕዝቡን በማስተባበር የሕዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ የልማት ሥራዎች መሰረታቸውን አይተናል።
የተመረቁት የፓርቲ ህንፃዎች በአባላትና ደጋፊዎች ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ በሲዳማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አማካይነት የተገነቡ ሲሆን በቁጥር ደረጃም ናቸው።
በአጠቃላይ በወረዳ ደረጃ 36፣ በክፍለ ከተማ 4 እንዲሁም በዞን ደረጃ 3 ሲሆኑ በቀጣይ ከሕዝቡ ጋር ተቀራርበን በምንሰራቸው የፖለቲካ እና የልማት ስራዎች የህንፃዎቹ ግንባታ ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ይሆናል።
በዋናነትም የህንፃዎቹ አሰራር አዳጊ ፍላጎቶቻችንን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ፣ በአመራራችን፣ አባላችን እና ደጋፊዎቻችን ሌት ከቀን ትጋት የተገነቡ፣ በሁሉም የፓርቲያችን መዋቅሮች ውስጥ ተቋማዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ ላለን ቁርጠኝነት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው።
ህንፃዎቹ ከፓርቲ ስራዎች በተጨማሪ የበጎ ፍቃድ ተግባራትን ጨምሮ ለሕዝባዊ አገልግሎቶች ክፍት የሚሆኑ ይሆናል።
በዚህ አጋጣሚ ይህ ተግባር እንዲሳካ ገንቢ ሚና የተጫወቱ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እያመሰገንኩ እንደ ሀገር የማንሰራራት ጉዟችንን የሚያጠናክሩ መሰል ስራዎችን መስራታችንን አጠናክረን እንድንቀጥልና በሁሉም መስኮች ጀምሮ የመጨረስ ባህላችንን እያረጋገጥን እንድንሄድ አደራ ለማለት እወዳለሁ።


