በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት እንዲሁም ወይዘሪት ናፍቆት ድሬ 2017 ዓ.ም ተወዳዳሪዎች ከወረዳ 7 ወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም አካሄዱ።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የወረዳ 7 ወጣት እና ስፖርት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወጣት ዳንኤል ተመስገን በክረምት በጎ ፍቃድ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማእድ የማጋራት እንዲሁም የአልባሳት ስጦታዎች እንደተበረከተ ገልፀው፤ በበጎ ፍቃድ ስራዎች አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዝ እርስ በእርስ የመተሳሰብ ባህልን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው ጠቁመዋል።
ወጣት ዳንኤል አያይዘውም በቀጣይም ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሰው ተኮር በሆኑ ስራዎች አቅመ ደካማ ወገኖችን የማገዝ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
የወረዳ 07 የወጣቶች ክንፍ ምክትል ሰብሳቢ ወጣት አባስ ነስረዲን የዛሬው ዝግጅት በዋነኝነት በበጎ ተግባር የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ አብሮነትን ማጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል።


