የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ እና ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ እንዲሁም ከሲነርጂ ፎር ኮሚኒቲ ዴቨሎፕመንት ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር የጎዳና ተዳዳሪነት እና ለምኖ አዳሪነት ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት እና ከአጋር አካላት ጋር በዛሬው እለት ውይይት ተካሂዷል ።
በሀገራችን የሚስተዋለውን የጎዳና ተዳዳሪነት እንዲሁም ለምኖ አዳሪነት ችግርን ለመፍታት መንግስት ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየሰራ ይገኛል በድሬዳዋ አስተዳደር በተለይም ዜጎች ከጎዳና ተዳዳሪነት እንዲሁም ከለምኖ አዳሪነት ችግር ተላቀው ስራ ፈጣሪ የሆነ ዜጋን ለማፍራት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ እና ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግረዋል ።
በእለቱም በድሬዳዋ አስተዳደር የጎዳና ተዳዳሪነት እና ለምኖ አዳሪነት ነባራዊ ሁኔታ እና ተፅእኖቹ ላይ ያተኮረ ሰነድም ቀርቧል ።


