ጳጉሜ 2 የህብር ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በአካል ብቃት እንቅስቃሴና በእግር ጉዞ መርሀግብር ተከበረ ።

የጳጉሜን ወር ቀናትን በተለያዩ ስያሜዎች በመሰየም በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ይታወቃል። ጳጉሜን 2 የህብር ቀን ምክንያት በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ ተካሄዷል።

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በእግር ጉዞ መርሀግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አርቢ ቡህ ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል ።

ደማቅ ከነበረው የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ በመቀጠል መነሻውን ምድር ባቡር ክበብ በማድረግ በአዲሱ የከዚራ የኮርደር ልማት መንገድ እስከ ነምበርዋን ጌም ዞን ድረስ በእግር ተጉዘዋል። በጌም ዞን የተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን አከናውነዋ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ አሊ ሴቶች የእግር ጉዞ እንዲያዘወትሩ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። ለሴቶች በእግር መጓዝ ለአካል እና ለአእምሮ ከሚሰጣቸው ጤና በተጨማሪ በወሊድ ጊዜ በምጥ እንዳይቸገሩ ከፍተኛ ጥቅም ሰላለው በእግር በመጓዝ ሊያዳብሩት ይገባል ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አርቢ ቡህ በበኩላቸው የእግር ጉዞውን አስመልክቶ እንደተናገሩት የእግር ጉዞ ማድረግ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም ስላለው የድሬደዋ ነዋሪ የእግር ጉዞን ባህሉ ማድረግ አለበት ብለዋል ።

የድሬደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመሪሮች ለሌሎች ምሳሌ በሚሆን መልኩ በሰፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋል ያሉት ምክትል ከንቲባ ሀርቢ የከፍተኛ አመራሩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ማድረጉ ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መነሳሳትን ይፈጥሪል ብለዋል ።

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በእግር ጉዞ ላይ የድሬዳዋ አሰተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የከተማው ነዋሪዎች የተለያዩ የማርሻል አርት ክለቦች እና ሌሎችም ተገኝተውበታል ።

Dire tv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *