በድሬዳዋ አስተዳደር ጳግሜ 2 “የህብር ቀን” በእግር ኳስ ጨዋታ ተከበረ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ጳግሜ 2 “የህብር ቀን” በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎችና በእግር ኳስ ጨዋታ ተከብራል።

በወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አስተናጋጅነት ዛሬ ጳጉሜን ሁለትን በማስመልከት ከማለዳ ጀምሮ በርካታ ስፖርታዊ ክንዉኖችን የተካሄዱ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታድየም የእግር ኳስ ጨዋታ ተከናውኗል።

70 ደቂቃ በፈጀዉ ጨዋታው ድሬ ጤና ቡድን ከድሬ ሰላም የተገናኙ ሲሆን በድሬ ጤና ቡን 5 ለ 0 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

ዉጤቱን ተከትሎ ድሬ ጤና በአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን የተዘጋጀዉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሏል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሀግብሩ ተሳትፎ ላደረጉ ተቋማት የእዉቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና በነገዉ እለት ከቀኑ 10:00 ላይ ድሬዳዋ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ከድሬ ምርጥ ቡድን ጋር በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታደየም የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *