የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አመራር እና ሰራተኞች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ በሜቄዶንያ አረጋውያን መርጃ ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል፤ በዓልንም በጋራ አክብረዋል።
በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ ቢሮው በየጊዜው ማዕከሉን እንደሚጎበኝ ገልፀው የዛሬ ፕሮግራምም በዋነኝነት በዓሉን በጋራ በፍቅር እና በመተሳሰብ ለማክበር መሆኑንን ተናግረዋል።
ሀገራችንን በተለያዩ ዘርፍች ያገለገሉ አረጋውያንን መንከባከብ እና ማስደሰት እንደሚገባም አቶ ብሩክ ጠቁመው በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚልኬሳ ሙሜ በበኩላቸው አረጋውያንን መንከባከብ እና መደገፍ እንደሚገባ ገልፀው በዓሉን በመተሳሰብ፣ በአብሮነት እና በፍቅር ከአረጋውያን ወገኖች ጋር ማክበራቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
የመቄዶንያ አረጋውያን መርጃ ማዕከል የድሬዳዋ ቅርንጫፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፆመ ሚናስ በበኩላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በየጊዜው ለማዕከሉ እያበረከተ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነው፤ ዛሬም በአልን በጋራ በማሳለፋቸው አመስግነዋል።
በዓሉን በጋራ ሲያከብሩ ያነጋገርናቸው የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው የአዲስ አመት በአልን በጉብዝናቸዉ ወቅት ለሀገራችን ውለታ ከዋሉ አረጋዉያን ጋር በጋራ በማሳለፋቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።


