ከንቲባው በዋሂል ክላስተር በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ለሁለት መቶ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ዛሬ አስረክበዋል።
ድጋፉ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከስቼንትሮ ኣዩቲፔር ሊ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አዲስ አመትን በማስመልስት የተደረገ ነው።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከቼንትሮ አዩቲ ፔር ሊ’ትዮፕያ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር አዲስ ዓመትን በማስመልከት በዋሂል ክላስተር ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አከናውኗል።
በአዲሱ ዓመት የትምህርት ማስጀመሪያ ወቅት ላይ ህፃናት በምንም ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ለ200 ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ቁሳቁስ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ፣ ለመቶ አቅመ ደካሞች እና ለአረጋውያን የምግብ ግብዓት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
በድጋፍ ስነ ስርአቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንዳሉት በድሬዳዋ የሚስተዋሉ ማህበራዊ ችግሮችን ከመቅረፍ አንፃር በመንግስት ከሚሰራው ሥራ ጎን ለጎን አንድነታችንን በማጠናከር የመተባበርና መተጋገዝ ባህላችንን በማጎልበት መሰል ድጋፎችን በግለሰብና በተቋማት ደረጃ ማበረታታት ይገባል ያሉ ሲሆን ‘ቼንትሮ አዩቲ ፔር ሊ’ትዮፕያ’ ግብረሰናይ ድርጅት እያደረገ ያለውን መልካም ተግባር አመስግነዋል።
ከግብረሰናይ ድርጅቱ ጋር በመተባበርም ድጋፉ ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲሆንና በገጠሩ ክፍል ለሚገኙ እድሜያችው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት እና ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች ለማድረስ እየሰሩ እንደሚገኙ ከንቲባው ጠቁመዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሐመድ በበኩላቸው ድርጅቱ በተለይም ህፃናት፣ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን በትምህርታቸው ከእንዲጠነክሩ ለማስቻል አወንታዊ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
የቼንትሮ አዩቲ ፔር ሊ’ትዮፕያ ግብረሰናይ ድርጅት መስራችና ባለቤት ልጅ እንዲሁም አሁን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፓውሎ ሎምባርዶ በበኩላቸው ድርጅታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የምግብ ግብዓት እና ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች ደብተር እና ቦርሳ በጥቅሉ ከ15 ሚለየን ብር በላይ የሚተመን ድጋፍ መበርከቱን አስረድተዋል።
ከ41 ዓመት በፊት በአባታቸው የተቋቋመውና ከምስራቅ ኢትዮጵያ በስቀር በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ላይ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኘው ድርጅታቸው በቀጣይ በድጋፉ የሚያግዛቸውን ህፃናት ብዛት ለማሳደግ እንዳቀደ ገልፀዋል።


