የአንድነት አርማ የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በርካታ ህዝብ የሳተፈበት የፎቶ አውደርዕይ በድሬዳዋ በኢትዮ አልያንስ ፍራንሲስ ማዕከል የፎቶ አውደርዕይ ተካሂዷል።
የፎቶ አውደ ርዕዩ በዋናነት የተዘጋጀው የአስተዳደሩ ህዝብ በህዳሴ ግድብ ታሪካዊ ተሳትፎውን እና ድጋፍ ለመዘከር ያለመ መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል።
በፎቶው አውደርዕዩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተው እንደተናገሩት የኢትዮጲውያን የውል ውጤት እና የጋራ ኩራት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በድል ተጠናቆ የዚህ ታሪክ ትውልድ አካል በመሆናችን ለመላው የአስተዳደሩ ነዋሪ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን በታላቅ ደስታ እና ስሜት ገልጸዋል።
የህዳሴ ግድብ ግንባታን ስንጀምረው ከድህነት እና ጉስቁልና በመላቀቅ ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር በጋራ ቃል ኪዳን በማሰር በራሳችን ሀብት እና ጉልበት ለመገንባት ከጫፍ እስከ ጫፍ በአንድነት በመቆም ዳግም የአድዋን ታሪክ መሰራት ችለናል ብለዋል።
በዚህ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ጅማሬ ላይ እንደምንገኝ እና ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን መሸጋገራችን ህያው ምስክር መሆኑን ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አሰፋም በበኩላቸው የዘመናት ቁጭት የሆነው ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለፍሬ በመብቃታች መደሰታቸውን ገልጸው በዛሬው እለት የተዘጋጀው የፎቶ አውደ ርዕይም የአስተዳደሩ ህዝብ በታሪካዊው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተሳትፎው ያደረገበትን እና የግድቡን የጉዞ ሂደት የሚያስቃኝ የፎቶ አውደርይ መከፈቱን አስረድተዋል።
አውደርዕዩም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጄ ጸጋዬ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ና መካከለኛ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በርካታ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።


