የታላቁ የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ምርቃትን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋው አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ትምህርት ቤት ካሳለፍነው እሁድ ጀምሮ የፎቶግራፍ አውደርዕይ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህም በፎቶ አውደርእዩ ተዘዋውረው ሲጎበኙ ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች በግድቡ ለምርቃት መብቃት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሀገራችን ህዝብ የይቻላል መንፈስን ያላበሰ ትልቅ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
እኛ ኢትዮጲያኖች በህብረትና በአንድነት በመቆም ሁሉንም ነገር ማሳካት እንደምንችል የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ በቀጣይ ለምንሰራቸው ትልልቅ የልማት ስራዎችም የህዳሴ ግድብ ከፍተኛ ብርታት ሰቶናል ሲሉ አብራርተዋል።
በአጠቃላይም አስተያየት ሰጪዎቹ ግድቡ በርካታ ተግዳሮቶችን በድል በማለፍ ለምረቃ መብቃቱ ከኢትዮጵያም አልፎ ለአፍሪካም ትልቅ ኩራት መሆኑን ጠቅሰው በግድቡ መመረቅ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።


