የግድቡን ምርቃት ምክኒያት በማድረግ በድሬዳዋው አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ትምህርት ቤት የፎቶግራፍ አውደርዕይ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያዊያን በአባይ ወንዝን ተጠቀሞ የመልማት የዘመናት መሻት ከረጅም ጊዜያት በኋላ በታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባት እውን ሆኗል።
ይህንን የአባይን ለሀገር እና ለህዝብ ፍላጎት ለማዋል በየዘመናቱ የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ የፎቶ አወደርዕይ በአሊያንስ ኢትዮፍራንሴስ ትምህርት ቤት ተከፍቶ እይታየ ይገኛል።
በኹነቱ ላይ ከታደሙት መካከል ወ/ሮ ኮከቤ ገበሬ በስደት በአረብ ሀገር ሳለች ለግድቡ ቦንድ መግዛቷን ገለፃ ከረጀም ጊዜ ልፋት በኋላ መመረቁ በተለይም የስራ እድል በመፍጠር ህገወጥ ስደትን በመከላከል በኩል ትርጉምም ያለው ለውጥ ይመጣል ብላ እንደምታምን ተናግራለች።
የብስራተ ገብርዔል አንደኛ እና 2 ደረጃ ትምህርት ቤት የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ህፃን መክሊት ጌትነት በበኩሏ የግድቡ መመረቅ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባት ገልፃ ወደ ፊት ለአገራችን በረካታ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ብላ አንደምታስብ ገልፃለች።
የፎቶግራፋ አውደርዕዩ ወንዙን ለልማት በማዋል በኩል በተለያየ ወቀት የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት እና ህዝቦች የነበራችውን ጥረት እና ፍሬን የሚያሳይ መሆኑን የገልፁት የኹነቱ ታዳሚዎች ኢትዮጵያውያን በህብረት ለአንድ አላማ ከተጋን የማናሳካው ግብ እንደማይኖር የህዳሴው ግድብ ህያው ምልክት ነው ብለዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አሰፋ የግድቡን ምርቃት አስመልክቶ በአሰተዳደሩ የድጋፍ ሰልፍና የተለያዩ ኹነቶች በቅርቡ እንደሚካሄዱ ተናግረዋል።


