የድሬዳዋ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም የተጀመረውና ለተከታታይ 5 አመት የሚተገበረው የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ባለፈው ዓመት ውጤታማ ስራዋች ማስመዝገብ መቻሉ የገለፁት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና ስትሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የ2018 በጀት አመት እቅዱን በማፅደቅ የገጠሩን ህብረተሰብ ብልፅግና ለማረጋገጥም 6መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙን ገልፀዋል።
ምክትል ከንቲባው አክለውም በ2018 በጀት አመት ቀደም ሲል የነበረውን የመንገድ እና የመስኖ ስራዋችን ይበልጥ አጠናክሮ ለመስራት ስትሪንግ ኮሚቴ የተናበበ እና የተቀናጀ ስራ ለመስራት በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ በስፋት መወያየታቸውን በመጥቀስ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የክትትልና የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
የቆላማ አካባቢዋች ኘሮጀክቱም በአስተዳደሩ ዝናብ አጠር በሆኑ ክላስተሮች የአደጋ ተጋላጭነታቸውን ለመቋቋም የሚያስችል ውጤት ማስገኘቱን ሰብሳቢው አቶ ሀርቢ ቡህ ገልፀዋል።
የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ(llP) ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ኢሳን ሙሴን በበኩላቸው ኘሮጀክቱ በአስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ቢሮዋችን ከማቋቋም እና ባለሙያዋችን በማማሏት ስራ መጀመሩን በመጥቀስ በትምህርት ፣በመንገድ ፣በጤናው ፣በመስኖ ውሀ በነበረው አፈፃፀም ቀደም ብሉ ከያዘው 250 ሚሊየን ብር በተመዘገበው ውጤት የነበረው በጀት በሦስት እጥፍ አድጎ እንደተያዘላቸው ጠቁመዋል።
የኘሮጀክቱ ማናጀር አቶ ኢሳን አክለውም በቆላማ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አርብቶ አደር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በሌማት ትሩፋት፣በአረንጓዴ አሻራ እና ከተረጂነት ወደ ረጂነት እንደ ሀገር የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካት ስትሪንግ ኮሚቴ ከመደበኛ እቅዳቸው ጋር በማጣጣም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


