የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ዜጎች ከመሰረታዊ ፍላጎት ባሻገር በክብር የመኖር ህልማቸውን ለመመለስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ዜጎች ከመሰረታዊ ፍላጎት ባሻገር በክብር የመኖር ህልማቸውን ለመመለስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው የመደመር መንግሥት መጽሃፍ ዛሬ ለንባብ በቅቷል። በመጽሐፉ የምረቃ መርሐ-ግብር ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የመጽሃፉ ደራሲና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣…


