የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን መቻል እና አንድነትን ለዓለም የገለጠ ነዉ ሲሉ የአስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ገለጹ

የድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መመረቅን አስመልክቶ በተከፈተው የፎቶ አውደርዕይ የመንግስት ሰራተኞች የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን መቻል እና አንድነትን ለዓለም የገለጠ ነዉ ሲሉ ገለጹ።

በፎቶ አውደርዕዩ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዲ በወቅቱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመሪዎቻችን በሳል ውሳኔ፣ በህዝባችን ኅብረት፣ ፅናትና መስዋዕትነት በመደመር እሳቤ የተገነባ የአሸናፊነታችን የብርሃን ዓምድ ነው ብለዋል።

2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ማንሰራራት የሚጀምርበት ተረጂነት የሚያበቃበት በሁሉም ዘርፎች ድል የምናስመዘግብበት የከፍታ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በተባበረ ክንድ በጋራ በአንድነት ሲቆሙ አርበኞች መሆናችንን ያረጋገጥንበት የጋራ አርማችን ነዉ ሲሉ በፎቶ አውደርዕይ ሲሳተፉ ያገኝናቸው አካላት ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *