በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን የንግድ፣ የኢንደስትሪና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናክሩ መሆናቸው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራ ልኡካን ቡድን ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም የድሬዳዋ አስተዳደር ልዩ ኢኮኖሚክ ዞንን፣ አማ የምግብ ዘይት ፋብሪካን፣ የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን የሚያመርተውን ድሬ ስቲል ፋብሪካን፣ ደረቅ ወደብን፣ በኢንደስትሪ መንደር የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክትን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በተፃፈው በመደመር ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭ እንዲሁም በአስተዳደሩ ድጋፍ ዘመናዊና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባውን እመርታ ቤተ-መፅሀፍን እንዲሁም ኮንቬንሽን ማእከልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

እንግዶቹ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው፤የልማት ስራዎቹ የከተማዋን የንግድ፣ የኢንደስትሪና የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናክሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *