“ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞቹን ከህልማቸው በማገናኝት ከድህነት ወደ ብልጽግና እያሸጋገረ ያለ ተቋም ነዉ ” ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የማህበረሰቡን የጋራ እድገትን እውቅና የሚሰጥበት ዓመታዊ የደንበኞች ኮንፍረንስ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአስተዳደሩ ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን በጎ ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዚህም ስራ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ሴቶች ፣ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች እና የእጅ ባለሞያዎች በመደበኛ ብድር የማግኝት እድል ያልነበራቸው አሁን በተቋሙ አማካኝነት እየበለጸጉ ነዉ ብለዋል።

ተቋሙ ዲጂታል የፋይናንስ አሰራሮችን በማበልጸግ ቀልጣፋ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረትም አስተዳደሩ ድጋፉን እንደሚጠናክር ገልጸዋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ አበበም በበኩላቸው ተቋሙ በመደበኛው የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ እና የፋይናንስ አካታችነትንም በተግባር የገለጠም ጭምር ነዉ ሲሉም ተናግረዋል ።

በዚህም ዜጎች ከትንሽ ስራ ተነስተው ከፍታ ላይ የወጡበት የስራ የህይወት አይነተኛ ለውጥ ነዉ ብለዋል።

በመርሃ ግብሩም ውጤታማ እና ሞዴል የሆኑ የብድር ደንበኞች የእውቅና እና የሽልማት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *