ክብርት ሚኒስትሯ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኮሚኒኬሽኑን ስራ በማዘመኑ ረገድ የሰራቸውን ስራዎችም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
” መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ” በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያስቀር ነው።
“ድሬ መሶብ” በመጀመሪያው ምዕራፍ ስድስት {6 } የአስተዳደሩ እና {4 } የፌደራል ተቋማትን የተለዩ 28 አገልግሎቶችን የሚሰጥ ይሆናል።


