በድሬዳዋ አስተዳደር የደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ የማፅዳት መርሀ-ግብር ተከናወነ

በመርሃ-ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከኃይማኖት አባቶች እና ከወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን የደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ አፅድተዋል።

ድሬዳዋ ሁሉም እምነቶች በፍቅር፣ በአብሮነትና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ መሆኗ የተገለፀ ሲሆን፤ እንደነዚህ አይነት በዓላትም ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እንደሚያጠናክሩ ተጠቁሟል።

በፅዳት ዘመቻው ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው የእስልምና፣ የፕሮቴስታንት እና የሌሎችም እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በድሬዳዋ ሁሉም በዓል በጋራ እና በአብሮነት እንደሚከበር የጠቆሙ ሲሆን በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም እና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በመርሀ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የካቢኔ አባላት፣ የፀጥታ አካላት፣ በጎ-ፍቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *