“ድሬ-መሶብ”የተገልጋዮች እንግልትን በመቅረፍ ቀልጣፋ እና ዲጂታል የሆኑ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ገለፁ

በድሬዳዋ አስተዳደር “ድሬ መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በዚህም በምርቃት በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ከመስጠቱ በተጨማሪ የዲጂታል ድሬን ጉዞ የሚያፋጥን መሆኑን አብራርተዋል።

ከንቲባ ከድር አያይዘውም “ድሬ መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት በአንድ ቦታ ላይ መስጠት የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ፤ይህም በመንግስት የሚቀርቡ አገልግሎቶች ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡ እንዲሁም ከብልሹ አሠራር የፀዱ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚያግዝ መሆኑን አመላክተዋል።

የኢፌድሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትአለም መለስ በበኩላቸው “ድሬ-መሶብ” የዜጎች የቅሬታ ምንጭ የሆነውን የአሰራር መጉላላት ለማሻሻል የሚበጅ ትልቅ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመሶብ ድሬ አንድ ማዕከል አገልግሎት በምዕራፍ አንድ በ10 ተቋማት 28 አገልግሎት እንደሚሰጥ የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ናቸው።

ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት ማዕከሉ 95% በመቶ መጠናቀቁን በማንሳት ከአስተዳደሩ የተመረጡ 25 ወንድ እና 39 ሴት በአጠቃላይ 64 ሰራተኞች ተዘጋጅተው በመጀመሪያው ምዕራፍ በማዕከሉ አገልግሎት ለመስጠት ክፍት መሆኑን አብስረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *